አዲስ አበባ ፣ ህዳር 14 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አርቲስት ደመረ ለገሰ የኢትዮጵያን ህልውና ለመታደግ ወደ ግንባር ሊዘምት መሆኑን ገለጸ።
የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ “ከእንግዲህ እኔ መከላከያን በግንባር ሆኜ ለመምራት ወደ ትግሉ ሜዳ እዘምታለሁ፤ ታሪክ ከሚያደንቃቸው የኢትዮጵያ ልጆች አንዱ ለመሆን የምታስቡ ሁሉ ለአገራችሁ ስትሉ ዛሬውኑ ተነሱ፤ ግንባር ላይ እንገናኝ!” ብለዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩን መልዕክት ተከትሎ በርካታ ታዋቂ ሰዎች፣ ፖለቲከኞችና ሌሎችም ግለሰቦች ተከትለዋቸው ለመዝመት ተዘጋጅተዋል።
“ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ቆራጥ መሪ እንዳላት በተግባር በማሳየታቸው ሁላችንም ኮርተናል፣ የአገራችንን ህልውና ለማስጠበቅም ተዘጋጅተናል” ያለው አርቲስት ደመረ፤ “ከማረሚያ ቤቶች የኦርኬስትራ ቡድን አባላት ጋር ወደ ዘመቻው ለመቀላቀል ተዘጋጅተናል” ብሏል።
ኢትዮጵያ በአሸባሪ ቡድን የተደቀነባትን የመፍረስ አደጋ ለመመከት የሁሉም ዜጋ ሃላፊነት በመሆኑ ለዘመቻው ተዘጋጅተናል ነው ያለው።
አርቲስት አያልነህ ሙላቱ በበኩሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት የወሰኑት ውሳኔ የቀደሙትን የኢትዮጵያ ጀግና መሪዎች ታሪክ አስታውሶናል ሲል ገልጿል።
ኢትዮጵያ በጠላት በተወረረችባቸው ጊዜ መሪዎች ግንባር ቀደም በመሆን ድል ማስመዝገባቸውን ገልጾ እርሳቸውም የአገራቸውን ክብር እንደሚያስጠብቁ አንጠራጠርም ማለቱን ኢዜአ ዘግቧል።
ኢትዮጵያ በዚያድ ባሬ ጊዜ ከሶማሊያ ጋር ባካሄደችው ውጊያ ፕሬዚዳንት መንግሥቱ ኃይለማርያም በጦር ግንባር ተገኝተው ሰራዊቱን በማበረታታት ድል እንዲመዘገብ ማድረጋቸውን አስታውሷል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!