Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ ደስታ ሌዳሞ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ዛሬ በይፋ የተመሰረተውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥትን በማስመልከት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ለረጅም ጊዜ በቅርበት መንግሥታዊ አገልግሎትን ለማግኘት የክልል እንሁን ጥያቄ ሲያነሱ መቆየታቸውን አስታውሰው÷ የህዝብን ጥያቄ አዳምጦ አፋጣኝ ምላሽ ባለመሰጠቱ አገልግሎት ለማግኘት ረጅም ርቀት መጓዝ አስገዳጅ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
በዚህም የጊዜና ገንዘብ ብክነት ይደርስ እንደነበር አስታውሰው፥ አሁን ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዘመናትን ያስቆጠረ ጥያቄያችሁ በለውጡ መንግሥት ምላሽ ማግኘቱ ከጭቁኖች ጎን ለቆሙ ሁሉ የጋራ ድል በመሆኑ፤ እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
ወንድም የሲዳማ ክልልም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በማጠናከር የጋራ አገራችንን በጋራ ለመገንባት ከጎናችሁ ይቆማልም ነው ያሉት፡፡
ክልል የመሆናችሁን ዕድል እና ያላችሁን ያልተነካ ፀጋ ተጠቅማችሁ የህዝባችሁን የተከማመሩ ችግሮችን ለመመለስ እንደምትጠቀሙበት እምነቴ የፀና ነው ብለዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version