አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ራስን በራስ የማስተዳደር ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ምላሹ የጦር አፈሙዝ ሳይሆን አስፈላጊውን ህጋዊ ምላሽ መስጠት ነው።
ዛሬ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝብ ለረጅም ጊዜ ሲያነሳው የነበረው የክልል እንሁን ጥያቄ እውን ሆኗል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች የህዝባችሁ ጥያቄ ፍሬ ላፈራበት ታላቅ ቀን በመድረሳችሁ የተሰማኝን ጥልቅ ደስታ እየገለፅኩ በራሴና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስም እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በፌስቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ።
ይህ ዕድል በክልላችሁ ያለውን ያልተነካ በርካታ የተፈጥሮ ሀብትና የቱሪዝም አቅም ይበልጥ በማልማት ክልላችሁን ብሎም ኢትዮጵያን የምታበለፅጉበት እንዲሆን ከልብ እመኛለሁመ ብለዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!