አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጀርመን በኢትዮጵያ የምታከናውነውን የልማትና የድጋፍ ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታወቀች።
የጀርመን የኢኮኖሚ ትብብርና የልማት ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዩርገን ሃርት እንዳስታወቁት ÷ በኢትዮጵያ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ድጋፍ የሚያስፈልገው ህዝብ ቁጥር አሻቅቧል።
በመሆኑም የጀርመን የኢኮኖሚ ትብብርና የልማት ሚኒስቴር ከለጋሽ አገራትና ከአውሮፓ ኅብረት ጋር በመቀናጀት በኢትዮጵያ የጀመረውን የልማት ትብብር የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል።
የጀርመን መንግሥት በኢትዮጵያ ለሚያከናውናቸው ሥራዎች የ100 ሚሊየን ዩሮ የልማት ትብብር በጀት መመደቡ የሚታወስ ነው።
ቃል አቀባይ ዩርገን ሃርት አክለውም ÷ “አሁንም ዓላማችን የአገሪቱን ህዝብ በተቻለን መጠን ተንቀሳቅሰን መደገፍ ነው” ብለዋል።
አፍሪካና ጀርመንን በንግድ፣ ኢንቨስትመንትና በግሉ ኢኮኖሚ ዘርፍ የሚያስተሳስረው የ (Compact with Africa) መርሃ ግብር አባል የሆነችው ኢትዮጵያ የጀርመን የልማት ትብብር ከፍተኛ ተጠቃሚ አገር መሆኗን ዶይቼ ቨለን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

