አዲስ አበባ፣ህዳር 15፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለመከላከያ ሰራዊት የ40 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
ከተደረገው ድጋፍ ውስጥ 8 ሚሊየን ብሩ የአይነት ሲሆን÷32 ሚሊየን ብሩ ደግሞ በጥሬ ገንዘብ የተደረገ ነው።
ድጋፉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ ለመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታዋ ማርታ ሊዊጂ አስረክበዋል።
ርዕሰ መስተዳደሩ ክልሉ ለመከላከያ ሰራዊቱ የሚያደርገው ሁለንተናዊ ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የክልሉ መንግስት በተለይ ከደጀንነት ባለፈ ህዝብና አመራሩ በግንባር ለመሰለፍ ቁርጠኛ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
የሐረሪ ህዝብ የህወሓት ጁንታን ለመደምሰስ የበኩሉን መወጣቱን ይቀጥላል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ክልሉ እስካሁን በ3 ዙር የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጉን ጠቁመዋል፡፡
በሌላ በኩል ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች የተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ለመከላከያ ሰራዊቱ ድጋፍ አድርገዋል።
በምስክር ስናፍቅ

