አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 4 ወራት ከወጪ ንግድ ከ1 ነጥብ 28 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የንግድ እና ቀጠናዎች ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።
የንግድ እና ቀጠናዎች ትስስር ሚኒስትር ገብረ መስቀል ጫላ በሰጡት መግለጫ÷በወጪ ንግዱ በለፉት አራት ወራት ውስጥ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ ከ1 ነጥብ 28 ቢሊየን ዶላር በላይ ማግኘት መቻሉን ተናግረዋል፡፡
አገሪቱ የተለያዩ ችግሮች ውስጥ ብትሆንም ይህንን ለመቋቋም በተደረገው ጥረት አበረታች ውጤት መገኘቱን ገልፀዋል፡፡
ገቢው በቅደም ተከተል ከግብርና 904 ሚሊዮን ዶላር፣ማኑፋክቸሪንግ 157 ሚሊዮን ዶላር፣ማዕድን 188 ሚሊዮን ዶላር፣ከኤክትሪክ ሽያጭ 30 ሚሊዮን ዶላር መሆኑንም ነው ያብራሩት፡፡
ባለፉት አራት ወራት የመሰረታዊ የሸቀጥ አቅርቦት ከአገር ውስጥ ምርትና ከውጭ በግዥ 286 ሚሊዮን ሊትር ዘይት፣7 ሚለዮን ኩንታል ስኳር ፣400 ሜትሪክ ቶን ስንዴ ለህብረተሰቡ ቀርቧል ሲሉም ጠቁመዋል፡፡
ተጨማሪ 400 ሺህ ሜትሪክ ቶን ስንዴ በግዥ ሂደት ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡
በፈትያ አብደላ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

