አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) አገር የማዳን ጉዳይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብቻ አይደለም ሲል ድምፃዊ አቡሽ ዘለቀ ተናገረ፡፡
ድምፃዊ አቡሽ ዘለቀ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበረዉ ቆይታ ፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ወደ ግምባር መዝመታቸውን አስታውሶ ÷ አገር የማዳን ጉዳይ ግን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብቻ አይደለም ብሏል፡፡
በዚህ ወቅት ሀገራችን በምትፈልገን ዘርፍ ሁላችንም ተሰላፊ መሆን አለብን ያለው ድምፃዊ አቡሽ ፥ ኢትዮጵያን ከአባቶቻችን የተረክብናት አገር ናት ፤ እኛ ደግሞ ለልጆቻችን ጠብቀን የማቆየት ሀላፊነት አለብን ነው ያለዉ፡፡
ለልጆቻችን የምናወርሳትን አገር ደግሞ ህልዉናዋ አደጋ ውስጥ በወደቀበት ወቅት ልንታደጋት ይገባል ብሏል፡፡
ሌላ አገር የለንም ፥ ያለችን አንድ አገር ናት፥ ያለችን አንድ አገር እንድትፍርስ አንፈቅድም ብሏል፡፡
እንደ ግለሰብ አገሬ ከእኔ የምትጠብቀውን ነገር ለማድረግ ዝግጁ ነኝ ፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ም ዝግጁ ሊሆን እንደሚገባም ድምፃዊ አቡሽ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

