አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የድል ተምሳሌት የነበረችውን አገራችን አሁንም ደማቅ የድል ታሪክ ታስመዘግባለች ሲሉ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋየ ተናገሩ።
ሚኒስትሯ አካባቢያቸውን በመጠበቅ ላይ የነበሩትን የኮልፌ ቀራኒዮና ልደታ ነዋሪዎችን በአካል በመገኘት አበረታተዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን ዳግማዊ የአድዋ ድልን ለመድገም እየተደረገ ባለው ትንቅንቅ በተለያዩ ግንባሮች መስዋዕትነትን እየከፈሉ ባሉበት በዚህ ወቅት ጨለማው አያግደንም ብርዱም አያስፈራንም በሚል መርህ የአካባቢያቸውን ፀጥታ ለማስከበር እየሰሩ ላሉት ስራም አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
ሚኒስትሯ ፥ ጥንትም የድል ተምሳሌት የነበረችውን አገራችን ዳግም በደማቅ የድል ታሪክ ላይ ለማስቀመጥ መከላከያን መደገፍና የአካባቢን ጸጥታ ማስጠበቅን ይበልጥ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግ መግለጻቸውን ከሚኒሰቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

