Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የጠቅላይ ሚኒስትሩ መዝመት ምንም ነገር ከአገር እንደማይበልጥ ያሳያል – የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ጦር ግንባር መዝመት በአርዓያነት እና በጀግንነት የተሞላና ሁሉም ለሀገሩ ቆራጥ መሆን እንዳለበት ያመላከተ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስተያየተቻውን የሰጡ የከተማዋ ነዋሪዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩ መዝመት እስከ መስዋዕትነት የሚዘልቅ ውሳኔ መወሰን እንደሚገባ ያሳየ ነው ብለዋል።

እኛ እምንኖረው አገር እስካለች ነው ስለዚህም ሁላችንም ጉልበት ያለው በጉልበቱ፣ ገንዘብ ያለው በገንዘቡ እውቀት ያለው በእውቀቱ ለአገሩ መቀጠል አስተዋፅኦ ማድረግ እንዳለበትም ገልፀዋል።

በአሁኑ ወቅት ከአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጪ የተደቀነብንን ችግር በህብረት እንሻገራለንም ነው ያሉት ነዋሪዎቹ።

ከዚህ ባሻገር የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተቀብለው ለመዝመት እንደተመዘገቡም ተናግረዋል።

በሚሊዮን አደም

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version