አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አሸባሪውን ቡድን የመደምሰስ ትግሉን ለመምራት ወደ ግንባር መዝመታቸው ከኢትዮጵያውያን አልፎ ለሌሎች አፍሪካውያን ጭምር ትልቅ መልዕክት ያስተላለፈ ነው ሲሉ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ይናገራሉ።
ኢዜአ ያነጋገራቸው የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን እንዳሉት፥ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡና በውክልና ለማስተዳደር ለሚፈልጉ አገራት ትምህርት ነው።
ዕጩ ዶክተር ፈንታሁን አዳሙ የህልውና ዘመቻው ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ነጻነትን ለማወጅ የምታደርገው ትግል መሆኑን ገልጸዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ ይህንን የሚያጠናክርና ለሌሎች አፍሪካውያን የሚያስተላልፈው መልዕክት ትልቅ መሆኑንም ይገልጻሉ።
የኢትዮጵያ ታሪካዊ የውጭ ጠላቶች ተላላኪ የሆነው አሸባሪውን ህወሃት አገር የማፍረስና ህዝብ የማጥፋት እኩይ ሴራን ማክሸፍ ዳግም የአድዋ ድል መሆኑንም አውስተዋል።
መላ አፍሪካውያንም ለውክልና ጦርነት የተነሳሱ እንደ አሜሪካ ያሉትን ጨምሮ የአንዳንድ ምዕራባውያንን ሴራ ለማክሸፍ ከኢትዮጵያ እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጎን በመሰለፍ ለነጻነታቸው ድምጻቸውን ማሰማት እንዳለባቸው አመላክተዋል።
ሌላኛው የዩኒቨርሲቲው መምህርት የኔወርቅ አለምነህ በበኩላቸው፥ ጦርነቱ በምዕራባውያን ድጋፍና ተሳትፎ እየተመራ የሚካሄድ ውሰብስብና አስቸጋሪ ቢሆንም በኢትዮጵያ አሸናፊነት እንደሚጠናቀቅ ከታሪክ መረዳት ተገቢ መሆኑን አውስተዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ግንባር መዝመትም ለሌሎች አፍሪካውያን የሚያስተላልፈው መልዕክት ትልቅ ከመሆኑም ባለፈ መላ ኢትዮጵያውያን በማነቃነቅና የሰራዊቱን ሞራል በመገንባት አኩሪ ድል ለማስመዝገብ እንደሚያስችል ጠቁመዋል።
“በጦር ግንባር ተገኝቼ ጦር እመራለሁ፤ ህዝቡ ይከተለኝ” ማለታቸው አሸባሪውን ቡድን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመደምሰስ ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንደሆነም አስረድተዋል።
“በዚህ ወቅት የመሪያችን ቃል ተቀብለን መሳተፍ የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥሪውን ተቀብሎ በሚችለው ሁሉ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለበት” ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

