አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በበጀት ዓመቱ በበጋ መስኖ 15 ሺህ ሄክታር መሬት በማልማት 500 ሺህ ኩንታል ምርት ለማምረት መታቀዱ ተገለፀ፡፡
የ2014 የምርት ዘመን ክልላዊ የበጋ ስንዴ ልማት ይፋዊ የማስጀመሪያ መርሀ ግብር በስልጤ ዞን በላንፉሮ ወረዳ ተካሂዷል።
በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር እንዳሉት፥ የግብርና ዘርፍ ለአገራችን ብሎም ለክልላችን የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት በመሆኑ ይህንን ዘርፍ ለማዘመንና ለማሳደግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው።
የሚያጋጥመውን ክፍተት ለመሸፈንም ሆነ ስንዴን በአገር ውስጥ በማምረት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በማዳን ለሌሎች የልማት ስራዎች በማዋል የአገራችንን እድገት ለማፋጠን እየተሰራ ይገኛል ማለታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በዞኑ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን ትኩረት በመስጠት 1 ሺህ 189 ሄክታር መሬት ለማልማት ግብ ተጥሎ እየተሰራ ይገኛል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

