Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ወደ ግንባር ሄደው ለመፋለም ዝግጁ መሆናቸውን የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፖርቲዎች አባላት ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ግንባር ሄደው ለመፋለም ዝግጁ መሆናቸውን የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት በቤላ ማገገሚያ ማዕከል በመገኘት ቁስለኛ የሰራዊት አባላትን ከጎበኙ በኋላ በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫውም አሸባሪው ቡድን በወረራቸው አካባቢዎች ዘርፈ ብዙ ኢሰብአዊ ጥፋቶችን አድርሷል፤ ይህንንም የጋራ ምክር ቤቱ በጽኑ እንደሚያወግዝ ገልጸዋል፡፡

የጦርነቱን አጠቃላይ አካሄድ በመገምገም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህዳር 14 ቀን 2014 ዓ.ም ወደ ግንባር እዘምታለሁ ማለታቸው በጋራ ምክር ቤቱ የሚደገፍ መሆኑን በመግለጫቸው ተናግረዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩን ፈለግ በመከተልም የምክር ቤቱ አባላት አገር የተደቀነባትን አደጋ ለማስወገድ ወደ ግንባር በመዝመት የአገርን ክብር እና ህልውና ለማስጠበቅ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላቱ በቤላ የሰራዊቱ ማገገሚያ ማዕከል በመገኘት ቁስለኛ የሰራዊቱ አባላትን ከመጎብኘት ባለፈ ምግብ ነክ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁስ በድጋፍ መልክ ማበርከታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version