Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመዲናዋ የሚገኙ የትምህርቱ ማኅበረሰብ አባላት ለተፈናቃዮች ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አበረከቱ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 14 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የሚገኙ የግል እና የመንግሥት ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና የትምህርቱ ማኅበረስብ በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ100 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ እና የአይነት ድጋፍ አበርክተዋል።
 
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በመስቀል አደባባይ በተደረገ የድጋፍ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር “ኢትዮጵያ አትፈርስም፤ ጠላት የተመኘው አይሰምርለትም” ብለዋል።
“ተማሪዎች እና የትምህርቱ ማኅበረሰብ ያደረጋችሁት ድጋፍ ለኢትዮጵያ ሕመም ሕክምና ነው፤ ኢትዮጵያ ትንሣኤዋን ስታበስር የተማሪዎች እና የትምህርቱ ማኅበረስብ አሻራ ስላረፈ ልትኮሩ ይገባል” ነው ያሉት።
 
ተማሪዎች ነፃነቷ እና የግዛት አንድነቷ የተጠበቀ አገር እንዲረከቡ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ጠቅሰው፥ ወቅቱ የሚጠይቀው መሥዋዕትነት እየተከፈለ እና ውጤቱም በገሀድ እየታየ መሆኑንም አንስተዋል።
 
ለአብነትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ አትፈርስም፣ የሚለውን በተግባር ለማሳየት ጦር ግንባር አቅንተዋል ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version