Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ ፍቃዱ ተሰማ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ 11ኛው የደቡብ ምህራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምሥረታን አስመልክተው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
 
የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
 
የውስጥ ቀንደኛ የሀገር ከሃዲዎችና የህዝብ ጠላቶች እንዲውም የዉጭ አበጋዞቻቸው በከፈቱብን የፊት ለፊትና የፕሮፓጋንዳ ጦርነት ውስጥ ሆነን የ11ኛውን የኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምስረታ ብስራት ሲንሰማ የተሰማኝ ሀገራዊና ህዝባዊ ኩራትና ደስታ የላቄ ነው፡፡ በዚሁ አጋጣሚ የትግል ውጤቱ ሰምሮ ይህን ራስን በራስ የማስተዳደር ነጻነትና ህጋዊ ዕውቅና ለመጎናጸፍ ለበቃው ለመላው የደቡብ ምህራብ ኢትዮጵያ ህዝብ በራሴና በመላው የክልላችን የፓርቲ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ስም የእንኳን ደስ አላችው መልዕክት አስተላልፋለው፡፡
 
በኢትዮጵያ ህዝቦች የትግል ታሪክ ውስጥ የማንነትና የአስተዳደር ነጻነት ጥያቄ እስከ ግማሽ ክፍለ-ዘመን ዕድሜ ያስቆጠረ ቢሆንም በሙሉ ቁመና ሊገለጽ የሚችል መልስ አልተገኘለትም፡፡ በ1987 ዓም ጸድቆ ሥራ ላይ የዋለው የኢፌድሪ ህገ-መንግሥት ራስን በራስ የማስተዳደር መብት የሚረጋገጡባቸው ህጋዊ ማዕቀፎችና ዕውቅና እንዲሰጥ የደነገገ ቢሆንም ባለ 27 ዓመቱ በህወሓት የበላይነት የተመራው ሥርሃት የማባበያና የማስፈራሪያ መሳሪያ አድርጎ ተጠቅሞበታል፡፡
 
የህዝቦች ግፊት፣ የለውጥ አመራሩ ቁርጠኝነትና የረዥም ዘመናት የትግል ውጤት የሆነው የኢትዮጵያ የለውጥ ምዕራፍ እልፍ አይላፋት ትሩፋቶችን ይዞ ብቅ ብሎሃል፡፡ ከነዚህ ትሩፋቶች መካከል ከአምስት አስርት ዓመታት ላልተናነሰ ጊዜ ተጓቶ ዛሬ ላይ ለደረሰው የማንነት ዕዉቅናና ራስን በራስ የማስታዳደር ጥያቄ እየተሰጠ ያለው መልስ ከፍተኛ ቦታ ሊሰጠውና እንደትልቅ ገድል ሊቆጠር የሚገባ ድል ነው፡፡
የለውጥ አመራሩ ባለፉት ሶስት ዓመታት የህዝቦች የዘመናት ጥያቄዎችን ለመመለስ ዘርፈ-ብዙ የሪፎርም ሥራዎችን አከናውኖሀል፡፡ የፖላቲካ ምዕዳሩን ከማስፋትና ለዴሞክራሲ ሥርሃት ግንባታ የሚያግዙ ህገዊ ማዕቀፎችና ሥርሃቶችን ከመዘረጋት አንጻር ረዥም ርቀት ተህዶሃል፡፡ ይህ ህደት ዛሬ ላይ ሰምሮ ለቁም ነገር በቅቶሃል፡፡ ሶስት ዓመት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ሁለት ተጨማሪ ክልሎች ህጋዊ ህውቅና አግኝተዋል፡፡
አዲሶቹ የሲዳማና የደቡብ ምህራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች የዚህ የስኬት ምዕራፍ ታሪክ ተቋዳሽ በመሆናችው በድጋሚ እንኳን ደስ አላችው፤ እንኳን ለዚህ ድል አበቃችሁ እላለሁ፡፡
 
በዚሁ አጋጣሚ የአጭር ጊዜ ስኬቶቻችን የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ግቦቻችን ትክክለኛነትና የአሸናፊነታችን አመላካች ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ስለሆነም ሀገራዊ ሉሃላዊነታችንንና ህዝባዊ እልውናችንን ለማስከበር እየተደረገ ያለውን ዘመቻ በአጭር ጊዜ አጠናቀን ዘርፈ-ብዙ ብልጽግና ለማረጋገጥ የጀመርነውን ጉዞ ከዳር ለማድረስ በትጋት መታገል ይጠበቅብናል፡፡
 
አንድነታችንን እንደ ብረት አጠናክረን የውስጥና የውጭ ጠላቶቻችንን አጉል እልም እንደምናመክን አንዳችም ጥርጥር የለንም፡፡
በመላው ህዝባችን የተባበረ ክንድ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!
 
የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ
 
ህዳር 2014
 
ፊንፊኔ
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version