አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መመሥረት ለኅብረ ብሔራዊ ፌዴራሊዝም ሥርዓት መጠናከር የተሰጠዉን ቁርጠኝነትን እንደሚያረጋግጥ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ፡፡
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦችየሆኑት የምዕራብ ኦሞ፣ የቤንች ሸኮ፣ የካፋ፣ የዳውሮ፣ የሸካ ሕዝቦችና የኮንታ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች ሕጋዊ ሂደቱን ጠብቀው በሕገ መንግሥቱ የተጎናጸፉትን መብት በመጠቀም 11ኛው የፌዴሬሽኑ አባል ክልል ሆነዋል። በዚሁ አጋጣሚ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ሕዝቦችን እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን።
የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ለበርካታ ዓመታት የክልልነት ጥያቄን ሲያነሡ ቆይተዋል፡፡ የለዉጡ አመራር ወደ ሥልጣን እንደመጣ ሲያነሱ የነበረው ጥያቄ ሕገ መንግሥታዊ መሆኑን በማመን ሕጋዊ አካሄድን ተከትሎ እንዲመለስ ጥሯል፡፡ በዚህ መሠረት ሕዝቡ በፍላጎቱ የራሱን ዕድል በራሱ እንዲወስን ተደርጓል፡፡ ዴሞክራሲያዊ በሆነ የሕዝበ ዉሳኔ ሂደት፣ ክልሉ በሕገ መንግሥቱ መሠረት አሥራ አንደኛ ክልል ሆኖ እንዲዋቀር ተደርጓል፡፡
በሕጋዊ፣ ሰላማዊና ሕገ መንግሥታዊ መንገድ የሚቀርብ የሕዝብ ጥያቄ ሁሉ የሚስተናገድበት ሥርዓት እየመሠረትን ነው። ትክክለኛው ፌዴራላዊ ሥርዓት የለውጡ ውጤት መሆኑንም የአዲሱ ክልል የምሥረታ ሂደት ጉልሕ ማሳያ ነው።
ለሕገ መንግሥቱም ሆነ ለፌዴራላዊ ሥርዓቱ አንዳች ቦታ ያልነበረዉና የዜጎችንም ጥያቄ በማፈን የኖረው አሸባሪዉ የሕወሐት ቡድን ከዉስጥና ከዉጭ ጠላቶቻችን ጋር በማበር ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚያደርገዉን እኩይ ተግባር ለመቀልበስ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ መንግሥት ጥሪዉን ያስተላልፋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

