Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የቤኒሻንጉል ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና የብልጽግና ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ወደ ግንባር ለመዝመት ወሰኑ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ግንባር ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባቀረቡት ጥሪ መሰረት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን እና የብልጽግና ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ወደ ግንባር ለመዝመት ወሰኑ።

የክልሉ አምስቱ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እና በፌዴራል ደረጃ ግንባሩን ለመቀላቀል የወሰኑ ከፍተኛ አመራሮች የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግምባርን በመቀላቀል ፊት ለፊት ሆነው የማስተባበር ስራን እንደሚያከናውኑ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢስሃቅ አብዱልቃድር ገልፀዋል።

ሴራውን ለመበጠስና አገርን ለማስቀጠል የአገር መከላከያ ሰራዊት፣ የክልል ፀጥታ ኃይልና ህዝባዊ ኃይሎች በቀረበላቸው የክተት ጥሪ መሰረት በሁሉም ግንባሮች ጠላትን እየተፋለሙ እንደሚገኙም ገልጸዋል።

ለሶስተኛ ዙር መከላከያ ሰራዊትንና የክልል የፀጥታ ኃይል ለመደገፍ 3 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር መሰብሰቡን ጽህፈት ቤት ኃላፊው ተናግረዋል።

የመከላከያ ምልመላና ተመላሾችን ምዝገባ እንዲሁም የደም ልገሳ ፕሮግራም በክልሉ ተጠናክሮ ቀጥሏል መባሉን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version