Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአርሲ ሕዝብ ለመከላከያ ሠራዊት ከ400 በላይ ሰንጋ በሬዎችን ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርሲ ዞን ሕዝብ ለጀግናው የአገር መከላከያ ሠራዊት ከ400 በላይ ሰንጋ በሬዎችን ድጋፍ አደረገ።
 
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙሳ ፉሮ በርክክብ ሥነስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ የዞኑ ህዝብ ያደረገው ድጋፍ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአገር በላይ ምንም ነገር የለም ብለው ወደ ግንባር በዘመቱበት ወቅት ላይ መሆኑ ለበለጠ ድል ያነሳሳል ብለዋል።
 
የዞኑ ሕዝብ የህልውና ዘመቻውን በአካል ከመቀላቀል ባለፈ ዘመቻው ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከ900 በላይ ሰንጋዎችን በሁለት ዙር ለአገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ በማድረግ ከጎኑ መሆኑን አሳይቷል ብለዋል።
በቀጣይም አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ አቅደን እየሰራን ነው ብለዋል።
በየደረጃው ያለው አመራርም ለዘመቻ የሚሆን ሀብት ከማሰባሰብ ጎን ለጎን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ፈለግ በመከተል ለመዝመት ተዘጋጅቷል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
በዞኑ የአሚኛ ወረዳ አስተዳደሪ አቶ ሁሴን እንድሪስ በበኩላቸው፥ የወረዳው ህዝብ በሁለተኛ ዙር 17 ሰንጋ በሬዎችን ድጋፍ ማድረጉን ገልጸው፥ ለሶስተኛ ዙር ደግሞ 18 ሰንጋ በሬዎችን እንዳስረከበ ነው የተናገሩት።
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አገራቸውን አስቀድመው ወደ ግንባር መዝመታቸው፥ በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ደረጃ ልዩ ግምት የሚሰጠው መሆኑን አስረድተዋል።
 
 
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version