Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

“ከቀደምት የወረስኩት አርበኝነትን እንጂ የድል አጥቢያ አርበኝነትን አይደለም” – በአርቲስት ደበበ እሸቱ

እልል በይ ኢትዮጵያ፣ የምስራች ኢትዮጵያ። ቆራጡ መሪ እምቢ ለሃገሬ፣ እምቢ ለዳር ድንበሬ ብሎ ለልእልናሽ ተከተሉኝ ብሎ ቀድሞልሻል።
“በኢትዮጵያ ለመጣ አንገቴ ይቆረጣል እንጂ እልደራደርም” ያለውን ቃሉን አክብሮ ጠላትን ሊፋለም በዘመቱብሽ ላይ ዘምቶባቸዋል።
ከምንም በላይ የኢትዮጵያ ደህንነት፣ ከማንም በፊት የወገን ነፃነት ብሎ ግምባር ሄዶልሻል።
የእምዬን ጥሪ ለዳግም አድዋ ድል ጠርቶ ሀገር ያልክ ተከተለኝ፣ ኢትዮጵያ ያልክ ለዘማቹ የሚያስፈልገውን ሲተርፍህ ሳይሆን የማይተካ ህይወቱን ለሰጠህ ሰራዊት ካለህ አስቀድመህ ለዘመተው ጀግና ሠራዊት አድርስ፣ ብሎ ቀድሟል።
ለሃገርህ አርበኛ ሁን እንጂ፣ የድል አጥቢያ አርበኝነት አይሞክርህ፣ ለከሃዲው ወንበዴ ርህራሄ የለሽ መሆን እራሱ የመረጠው አካሄድ ነው፣ በመሆኑም እሳትን በእሳት ነው ምላሹ።
ሽምግልናን የናቀ፣ ምክርን እምቢ ያለ፣ እራሱን በከንቱ ያጀገነ፣ ከንቱነቱን እንደ ድል አድራጊ የመረጠ፣ ያጎረሰውን እጅ የነከሰ፣ ውልታ የማያውቅን እብሪተኛ በኢትዮጵያ ላይ ያመፀን እኩይ ወንበዴ ላንድዬና ለመጨረሻው መዳረሻውን ግብአተ መሬት ማድረግ ብቻ ነው መርሃችን ሊሆን የሚገባው።
ኢትዮጵያን ያልን የጥሪው አቤት ባይና አለሁ እለጥቅሃለሁ በማለት ጨርቄን ማቄን ሳንል የዘመቻው አካል መሆንን በተግባር እናረጋግጥ።
ለመወሰን አማራጭ አያስፈልገንም፣ የሚያስፈልገን ኢትዮጵያዊነትን መተግበር ነው።
“ስንወለድ ኢትዮጵያዊ፣ ስንሞት ኢትዮጵያ” እንዲሉ!
ከቀደምት የወረስኩት አርበኝነትን እንጂ፣ የድል አጥቢያ አርበኝነትን አይደለም።
በመሆኑም ጥሪውን ተቀብዬ ከደጀንነት ባለፈም ጀግኖች በዋሉበት ለመዋል ተዘጋጅቻለሁ!
ምንጭ፡-ኢዜአ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version