አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ የሚያካሂዱትን ጣልቃ ገብነት እና ሐሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ መገናኛ ብዙኃንን የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፍ በአሜሪካና እንግሊዝ ኤምባሲ ዛሬ ተካሄዷል።
የሰልፉ ተሳታፊዎች ሩሲያ ኤምባሲ በደረሱበት ወቅትም ሩሲያ ለኢትዮጵያ እያደረገች ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
መነሻውን አራት ኪሎ በማድረግ ወደ እንግሊዝና አሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ አባት አርበኞች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈውበታል።
ሰልፉ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ መካሄድ የጀመረ ሲሆን የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ለ10 ደቂቃ ያህል መብራት በማብራትና ድምጽ በማሰማት የተቃውሞ ሰልፉን አጅበውታል።
በተቃውሞ ሰልፉ የተሳተፉት የህብረተሰብ ክፍሎች የኢትዮጵያን እውነት ለመደበቅና እንዳላዩ ሆነው ለማለፍ ለሚፈልጉት ምእራባውያንና ሚዲያዎቻቸው በቀን ፋኖስ በማብራት እውነታውን መደበቅ እንደማይችሉ አስታውቀዋል።
ነዋሪዎቹ ከቀኑ 6:30 ከአራት ኪሎ ተነስቶ በአሜሪካ ኤምባሲ ድምጻቸውን አሰምተዋል፡፡
በሰልፉም ÷ ጣልቃ ገብነት ኢ-ዲሞክራሲያዊነት ነዉ ፤ #በቃ ፣ (ቢቢሲ፣ ሲኤን ኤን) የሀሰት ዘገባችሁን አቁሙ፤ አትዮጵያ ድል ታደርጋለች እና አንድ አፍሪካ የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮች በኤምባሲው ተስተጋብቷል፡፡
በተጨማሪም ÷ በተቃውሞ ሰልፉ “እኛ ኢትዮጵያውያን በባእዳዊ ግዛት ያልተገዛን ነፃ ሕዝቦች ነን” አሜሪካ እና ምዕራባውያን ከኢትዮጵያ እጃችሁን አንሱ፣ የሚሉ መልእክቶች ከሰልፈኞቱ ተላልፈዋል።
በሀበነዮም ሲሳይ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
