አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሽብርተኞቹ ህወሓትና ሸኔ ጋር የህቡዕ ትስስር በመፈፀም አገር በማተራመስና በማፍረስ ሴራው ውስጥ ለመሳተፍ ዝግጅት እያደረጉ ያሉ ተጠርጣሪዎችን በህግ ቁጥጥር ስር የማዋሉ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ከህወሓትና ሸኔ የጥፋት ተልዕኮ ተቀብለው በአዲስ አበባ ከተማ ሁከት፣ ግርግርና ሽብር ለመፈፀም ዝግጅት እያደረጉ ባሉ ተጠርጠሪዎች ላይ ድንገተኛ ፍተሻ በማድረግ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና ሰነዶችን መያዝ መቻሉን ለመረጃው ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን አረጋግጠዋል፡፡
በዛሬው ዕለትም በአዲስ አበባ ከተማ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሰባት ከጁንታው ጋር ትስስር አላት በሚል ከአካባቢው ህብረተሰብ በደረሰ ጥቆማ በመኖሪያ ቤት በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ሁለት ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች ከ60 መሰል ጥይቶች ጋር እንዲሁም ሁለት ሽጉጦች ከ20 መሰል ጥይቶች ጋር በፀጥታ አካላት መያዛቸውን ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁት የመረጃ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ በዚሁ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወራዳ ሁለት በሚገኘው አትላስ ሆቴል ውስጥ ለሶስት አመታት ያህል አልጋ በመያዝ ከሽብርተኛው ሸኔ ጋር በህቡዕ በመገናኘት ተልዕኮዎችን ሲያስተባብር የነበረ አንድ ተጠርጣሪ ግለሰብም በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
ተጠርጣሪው ባረፈበት ሆቴል ውስጥ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ አድንዛዥ ዕፅ፣ ሶስት ኮምፒዩተሮች፣ ሁለት ፕሪንተሮች፣ ሰባት የተለያዩ ማህተሞች፣ አንድ ላፕቶፕ እና አንድ ትልቅ ማይክ ተይዟል።
ከዚህ ባለፈም በማህበራዊ ትስስር ገጾች ለመልቀቅ ያዘጋጀቸው የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ሰነዶች ከሁለት ግብረአበሮቹ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉን በማስረጃነት የተያዙ ፎቶዎችን አያይዘው ለመረጃው ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን ልከውልናል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

