አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ግንባር መዝመት ሁሉም ነገር ከአገር በታች መሆኑን አመላካች ነው ሲሉ የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
ነዋሪዎቹ የክተት ጥሪውን ተቀብለው ዘመቻውን ለመቀላቀል መወሰናቸውንም ተናግረዋል።
የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት አሜሪካ እና አንዳንድ ምዕራባውያን አገራት አሸባሪውን ሕወሓት ፈረስ በማድረግ ኢትዮጵያን ለማንበርከክ እየሰሩ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡
የነፃነት ተምሳሌት የሆነችውን ኢትዮጵያን ማንበርከክ መላው አፍሪካውያንን ማንበርከክ ነው ብለው በማሰብ አገራችንን እየወጉ መሆናቸውን የተናገሩት ነዋሪዎቹ፥ መላው የአገራችን ህዝብ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጎን ሊሰለፍ ይገባል ብለዋል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ግንባር መዝመት ሁሉም ነገር ከአገር በታች መሆኑን አመላካች በመሆኑ የእርሳቸውን ፈለግ ተከትለው ለመዝመት መዘጋጀታቸውንም ነዋሪዎቹ የገለጹት።
ምዕራባውያን በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ ላይ ተላላኪ መንግስት ለመመስረት ሽፍጥ ሲፈፅሙ መቆታቸውን የገለፁት ነዋሪዎቹ፥ ከዚህ በኋላ በመረጥነው እንጂ በተላላኪ መንግስት እንደማንመራ ሊያውቁ ይገባል ነው ያሉት፡፡
በማቴዎስ ፈለቀ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

