Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢሚሬትስ ቀይ ጨረቃ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ቀጥሏል

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች በሰብዓዊ ቀውሱ ለተጎዱ ኢትዮጵያውያን በኢሚሬትስ ቀይ ጨረቃ በኩል የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ መቀጠሏን ገለጸች።
የጤና ሁኔታን ለማሻሻልና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሥርጭትን ለመከላከል የሚረዱ የህክምና መሣሪያዎች አቅርቦትን ጨምሮ ከፍተኛ መጠን ያለው የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ዛሬ አዲስ አበባ ገብቷል።
የኢሚሬትስ ቀይ ጨረቃ ዋና ጸሃፊ ዶክተር መሀመድ አቲክ አል-ፋላሂ አገራቸው የኢትዮጵያ ህዝብን ሰብዓዊ ፍላጎት ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።
ከዚህ አኳይ የኢሚሬትስ ቀይ ጨረቃ ካደረገው የህክምና ድጋፍ ባሻገር የምግብ፣ አልባሳት፣ ሌሎች ቁሳቁስ እና ሰብዓዊ ድጋፍ ማቅረቡን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ዛሬ የተደረገው ድጋፍ በኢትዮጵያ በተፈጠረው ቀውስ ለተጎዱ ዜጎች በተለይም ሴቶች እና ህፃናትን ለመርዳት የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እያደረገች ያለው ጥረት አካል መሆኑን ገልጸዋል።
የኢሚሬትስ ቀይ ጨረቃ የኢትዮጵያን ሰብዓዊ ሁኔታ በቅርበት ይከታተላል፤ አገራዊ የሰብዓዊ ጥረቶችን እንደሚደግፍ ዋና ጸሃፊው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version