አዲስ አበባ፣ህዳር 16፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የክልሉ መንግስትና ህዝብ የሰጣቸውን ሀላፊነት በአግባቡ እንደሚወጡ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ተሿሚዎች ተናገሩ፡፡
ለዘመናት የዘለቀውን የአዲሱን ክልል ሁለንተናዊ ችግሮች ለመቅረፍ በሚደረገው እንቅሰቃሴ ውስጥ ህብረተሰቡ ሊያግዘን ይገባልም ብለዋል፡፡
የክልሉ ደንና አካባቢ ጥበቃ ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ኢንጅነር አሰራት ገብረማሪያም እንዲሁም የውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ ኢንጅነር በየነ በላቸው በሰጡት አስተያየት ከመንግስትና ከህዝብ የተሰጣቸውን አደራ እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመቁጠር የክልሉን ችግሮች ደረጃ በደረጃ ለመቅረፍ ጥረት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
ያለ ህብረተሰቡ ተሳትፎ ሊሳካ የሚችል ተግባር ባለመኖሩ ህብረተሰቡ በሁሉም መልኩ ከክልሉ አመራሮች ጎን እንዲቆምም ጠይቀዋል፡፡
በክልልነት የመደራጀት የረጅም ጊዜ የህዝቡ ጥያቄ እውን እንዲሆን ለተጉ አካላትም ተሿሚዎቹ ምስጋና ማቅረባቸውን ከደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

