Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የመኖሪያ ቤታቸውን ሽጠው ለመከላከያ ሰራዊት 2 ሚሊየን ብር የለገሱት እናት

አዲስ አበባ፣ ህዳር 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወ/ሮ ቦጋለች ከበደ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሀገር ሉአላዊነትን ለማስከበር ወደ ግንባር ዘምተው ዝም ብዬ ማየት የለብኝም በማለት የመኖሪያ ቤታቸዉን በመሸጥ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የ2 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ።
አገር ከሌለ ሁሉም ነገር የማይቻል በመሆኑ፤ በቤት ለመኖር ቅድሚያ አገርን በክብር ማኖር ይገባል ያሉት ወ/ሮ ቦጋለች÷ ቤታቸውን ሸጠው ለኢትዮጵያ ህልውና እየተፋለመ ለሚገኘው ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለግሰዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version