Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ወደ ግንባር ለሚዘምቱ የኢዜማ አመራሮች ሽኝት ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአዲስ አበባ ከተማ ወደ ግንባር ለሚዘምቱ የኢዜማ አመራሮች በዛሬው ዕለት አሸኛኘት ተደርጓል።
የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሽዋስ አሰፋ አመራሩ ወደ ግንባር በመሄድ ሰራዊቱን ያበረታታል አባላቱ ደግሞ ወደ ስልጠና በመግባት መከላከያውን ተቀላቅሎ ለአገሩ እንደሚቆም ገልጸዋል።
ኢዜማ የኢትዮጵያን ነጻነት ለማስጠበቅ ሁልጊዜም ከፊት ይሰለፋልም ነው ያሉት።
ወደ ግንባር የሚዘምቱ አመራሮችም ኢትዮጵያ ፈተና ውስጥ በምትሆንበት ጊዜ መስዋዕትነት መክፈል ከጥንት ጀምሮ በደማችን ያለ መሆኑን በመጥቀስ፥ በድል እንደምንመለስም እርግጠኞች ነን ብለዋል።

የኢዜማ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከዚህ ቀደምም የተለያዩ የኢዜማ አባላት ወደ ግንባር መሄዳቸውን ገልጸው የሄዱት ግን ኢዜማ ስለሆኑ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ስለሆኑ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያን ለመጪው ትውልድ ማስረከብ የሁላችንም ግዴታ ነው ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፥ እዚህ የተቀረው አባልና ሌሎች ኢትዮጵያውያንም ለዘማቾች ስንቅ በማዘጋጀት ደጀን እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

በዘመን በየነ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version