አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአገራቸው ክብር እና ሉዓላዊነት የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ኢትዮጵያን በተለያዩ አገራት የወከሉ አምባሳደሮች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች ተናገሩ።
የአምባሳደሮች እና የሥራ ኃላፊዎች ዓመታዊ ስብሰባ እየተካሄደ ነው።
“ከመሪያችን፣ ለአገራችን ክብር ከሚዋደቀው የአገር መከላከያ ሰራዊት እና ከመላው የፀጥታ ኃይላችን ጎን መቆማችንን ስንገልፅ ታላቅ ኩራት እና ክብር ይሰማናል” ነው ያሉት።
የአገራቸውን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ወቅቱ የሚጠብቀውን የዲፕሎማሲ ሥራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡
ለአገር መከላከያ ሰራዊት የገንዘብ ልገሳ ያደረጉ ሲሆን በቀጣይም የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን እንገልፃለን ብለዋል።
በነገው ዕለትም የደም ልገሳ ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!