አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ ) ለሀገርና ለህዝብ ህይወቴን ለመስጠት ዝግጁ ነኝ ከጠቅላይ ሚኒስትሬ ጋርም እዘምታለሁ ሲሉ ድጋሜ ለመዝመት የተዘጋጁት ዘማች አርሶ አደር ተናገሩ፡፡
አርሶ አደሩ ከቁስለኝነት አገግመው ድጋሜ ለመዝመት መዘጋጀታቸውም ተገልጿል፡፡
በጎንደር ዙሪያ ደረስጌ ማርያም ደብር ቀበሌ የሚኖሩት 50 አለቃ ክንዴ ደርበው የቀድሞ ጦር ሰራዊት አባል ናቸው።
ከዚህ ቀደም በደቡብ ጎንደር ግምባር ዘምተው ቆስለው የተመለሱ ሲሆን÷ ሀገሬ ተወራ እኔ አልተኛም በማለት የአካባቢውን ምልምል አርሶ አደሮች ወታደራዊ ስልጠና ሲሰጡ ቆይተዋል።
አሁን ደግሞ ያሰለጠንኳቸው ዘማቾች ዝግጁ ሆነዋል የአካባቢው ህብረተሰብና የመንግስት ተቋማት ሰራተኞች ሰብሌን ሰብስበውልኛል ከጠቅላይ ሚኒስትሬ ጋር ድጋሜ ለመዝመት ተነስቻለሁ ብለዋል።
ወራሪውን ቡድን ለመደምሰስ አቅም ያለው ሰው ሁሉ ከመሪያችን ጋር ሊንዘምት ይገባል ሲሉ ጥሪ ያስተላለፉት አርሶ አደሩ ምትክ ለሌላት ለሀገሬ የምሰስተው ነብስ የለኝም ደጋግሜ እዘምታለሁ ብለዋል፡፡
ከጎንደር ፋና ኤፍኤም ባልደረቦች
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!