Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አሸባሪው የህወሓት ቡድን በትምህርት ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል

አዲስ አበባ፣ህዳር 18፣2014 (ኤፍ ቢሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአማራና በአፋር ክልሎች ባካሄደው ወረራ በትምህርት ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፥ የአሸባሪው የህወሓት ቡድን በአማራ ክልል በትምህርት ቤቶች ላይ ባደረሰው ውድመት 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆነዋል።
አሸባሪው ወራሪ ቡድን ከፍተኛ ጉዳት ካደረሰባቸው ማህበራዊ ተቋማት መካከል የትምህርት ዘርፍ አንዱና ዋነኛው ነው ብለዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታዋ እንዳብራሩት፥ በአማራ ክልል አምስት ዞኖች 1 ሺህ 660 ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ውድመት ደርሶባቸዋል።
ከነዚህም ውስጥ 277 ትምህርት ቤቶች እና ሁለት የመምህራን ኮሌጆች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል።
በዚህም 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ውጭ የተደረጉ ሲሆን÷ 47 ሺህ መምህራን ከሥራ ተፈናቅለዋል ብለዋል፡፡
በአፋር ክልል ደግሞ እስካሁን ባለው መረጃ 455 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ነው የገለጹት፡፡
በመንግሥት በኩል በትምህርት ዘርፉ የደረሰውን የጉዳት መጠን እና በቀጣይ ለሚሰራው ሥራ ጥናት እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።
ከአጋር ድርጅቶች ጋር ለመሥራትም ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ነው ሚኒስትር ዴኤታዋ የተናገሩት፡፡
አሸባሪው ወራሪ ኃይል የሚፈጽመውን ወረራ እና ውድመት ለመቀልበስ በአሁኑ ወቅት የተሟላና ከፍተኛ የማጥቃት እርምጃ እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመው፥ ደጀኑ ህብረተሰብም እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version