አዲስ አበባ፣ ህደፋር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አምስት ሴት ጋዜጠኞች ከሶስት መቶ ሺህ ብር በላይ በማሰባሰብ ለህልውና ዘመቻው የስንቅ አስረከቡ፡፡
ከአዲስ አበባ የተውጣጡ ሴት ጋዜጠኞች አስተባባሪ ወይዘሮ አዜብ ታምሩ እንደተናገሩት÷ ከራሳቸውና ከወገኖቻቸው ባሰባሰቡት 350 ሺህ ብር 130 ኩንታል በሶ አዘጋጅተው ለህልውና ዘመቻው እንዲሆን ለሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር አስረክበዋል።
እኛ ግንባር ለሚዋደቀው ሰራዊት የኋላ ደጀን ነን በሚል ወኔ በቀጣይም ድጋፉ ተጠናሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ወልደ አማኑኤል÷ በተለይ የሴቶች ሚና የላቀ በመሆኑ እናንተ ለሌሎች ሴቶች አርአያ ናችሁ በለዋል፡፡
በእታገኝ መኮንን
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

