Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአዲስ አበባ አማራ ወጣቶች ማህበር የመድሀኒት አልባሳት እና የምግብ ግብአት ለወገን ጦር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ህዳር 18፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በአዲስ አበባ አማራ ወጣቶች ማህበር የመድሀኒት አልባሳት እና የምግብ ግብአት ለወገን ጦር ድጋፍ አድረጓል
ድጋፉ 2.5 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው ለወገን ጦር የሚውል እንደሆነም ተገልጿል።
ከጀግናው የመከላከያ ሰራዊት እና ልዩ ሀይል ጋር በጥምረት እየተፋለሙ ለሚገኙ ፋኖ እና ሚሊሻ አባላት የሚውለው ድጋፉ በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
ድጋፉን ያስረከቡት የአዲስ አበባ አማራ ወጣቶች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ዘነበ በለጠ እንዳሉት የማህበሩ አባላት በወቅታዊ የሀገራችን ጉዳይ ከዚህ ቀደምም መሠል ድጋፎች ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሠው በቀጣይም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።
ድጋፉን የተቀበሉት የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ወ/አማኑኤል ለተደረገዉ ድጋፍ አመሥግነው መሠል እርዳታዎች የህልውና ዘመቻው በድል እስኪጠናቀቅ መደገፍ ይገባል ብለዋል።
በኤልያስ ሹምዬ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version