አዲስ አበባ፣ህዳር 18፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ከባለሐብቱ ከነጋዴውና ከነዋሪው ማኅበረሰብ በማሰባሰብ ለጀግናው የመከላከያ ሠራዊት እና ለአማራ ልዩ ኃይል የሚውል 20 የእርድ ሰንጋዎች እንዲሁም አልባሳት አስረክቧል፡፡
የሰሜን ዕዝ ጠቅላላ ሆስፒታል የሎጀስቲክስ አስተባባሪ ሌተናል ኮለኔል ሰብለ ሙሉጌታ ÷ የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎችና የአካባቢዋ ህዝብ እያደረገው ላለው ደጀንነት ምስጋና አቅርበው÷ በቀጣይ የአሸባሪውና ወራሪው ኃይል ለመጨረሻ ጊዜ እስኪደመሰስ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል፡፡
በርክክብ ሥነ-ስርዓቱ የባህርዳር ከተማ ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳህሉ፣ በም/ከንቲባ ማዕረግ የባህርዳር ከተማ አስተዳደር የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ብርሃን ንጉሴ፣ የአማራ ክልል ፖሊስ ም/ኮምሽነር ሐብታሙ ሲሳይ እንዲሁም የሰሜን ዕዝ ጠቅላላ ሆስፒታል የሎጀስቲክ አስተባባሪ ሌተናል ኮለኔል ሰብለ ሙሉጌታ መገኘታቸውን ከአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

