Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ጦር ግንባር መዝመት የድል ሞራል ነው – ዶ/ር በድሉ ወቅጅራ

 

አዲስ አበባ፣ህዳር 19፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ጦር ግንባር መዝመት የድል ሞራል እንደሆነ መመህርና ደራሲ ዶክተር በድሉ ወቅጅራ ተናገሩ፡፡

ዶክተር በድሉ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ጦር ግንባር መዝመት የድል ሞራል እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምዕራባዊያን ያቃታቸውን የኢትዮ ኤርትራን ግንኙነት ወደ ሰላም እንዲመለስ ያደረገ መሪ መሆኑን የሚያስታውሱት ዶክተር በድሉ÷ በምስራቅ አፍሪካ በአጭር ጊዜ ከዚህ በላይ ሌላ ተጽዕኖ እንዴት ሊኖር ይችላል ብለዋል፡፡

አንዳንድ ምዕራባዊያን የጠቅላይ ሚኒስትሩን መዝመት ስለማይፈልጉት በየሚዲያዎቻቸው የሰላም ኖቬል ተሸላሚው ዘመቱ ማለታቸውን ገልጸው÷ ይህ ርምጃ ጭራሽ ህዝቡን አንድ አድርጎ ከመሪው ጎን የሚያሰልፍ እና ተቀባይነትንም የሚጨምር ነው ብለዋል፡፡

የኖቤል ሽልማትን መቀበል ሀገርን አሳልፎ መሰጠት ፤ የሃገር ሉዓላዊነትን መሸጥ አይደለም ብለዋል፡፡

የምዕራባዊያን አላማ ፍላጎታቸውን አስፈጻሚ የሆነ አካል ማግኘት ነው የሚሉት ዶክተሩ÷ የፓን አፍሪካኒዝም ጫና እየመጣ ሲያዩት ማእቀብ ጣልበት፣ወረረው አፍርሰው የሚለውን ተፈጥሯዊ ማንነታቸውን ማሳየት መጀመራቸውን ይናገራሉ፡፡

ህዝባዊ ምላሽ የሚፈልገው ጦርነቱ ብቻ ሳይሆን የውጭ ጫናውም እንደሆነ ከፋና ብሮድካስቲን ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል፡፡

በሻምበል ምህረት

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version