Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የላፍቶ ክ/ከተማ ለሰራዊቱ 10 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ላፍቶ ክፍለ ከተማ ግንባር ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊት 10 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት የምግብ ድጋፍ አድርጓል።
 
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ነፃነት ዳባ÷ ክፍለ ከተማው እስካሁን የሽብር ቡድኑን ህወሓት እየተፋለመ ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊት ከ300 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።
 
አሸባሪው እና ወራሪው ህወሓትእስኪደመሰስ ድረስም የህዝቡ ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት ወይዘሮ ነፃነት።
 
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ በበኩላቸው÷ ህዝቡ ከሰራዊቱ ጎን በመቆም የደጀንነት ተግባሩን እየተወጣ መሆኑን አውስተዋል።
 
በተባበረ ክንድ ጠላትን በመደምሰስ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ መስዕዋትነት ለሚከፍለው ሰራዊት የሚደረገው ድጋፍ ተጥናክሮ እንደሚቀጥልም አንስተዋል።
 
ድጋፉን የተረከቡት ሌተናል ኮሎኔል ለችሳ መርጋሳ÷ የህዝቡ የማያቋርጥ የደጀንነት ተግባር ለሰራዊቱ ትልቅ ጥንካሬ ነው ብለዋል።
 
ጠላት መውጫ አጥቶ በወገን ጦር እየተቀጣ ነው ያሉት ሌተናል ኮሎኔሉ÷ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እያደረገ ላለው ሁለንተናዊ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
 
በሳመራዊት የስጋት
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version