Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአንድ ወር በተፈፀመ ወንጀል ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ጉዳት ደርሷል- ኤሌክትሪክ አገልግሎት

አዲስ አበባ፣ ህዳር 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጥቅምት ወር ብቻ በተፈፀሙ ወንጀሎች ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ጉዳት እንደደረሰበት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡
አገልግሎቱ÷ በ2014 በጀት ዓመት ጥቅምት ወር በተፈፀመ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ግብዓትና የኃይል ስርቆት ላይ 1 ሚሊየን 437 ሺህ 967 ብር ጉዳት ደርሶብኛል ብሏል፡፡
ጉዳቱ የደረሰው በኤሌክትሪክ ኬብል ስርቆት፣ በኃይል ስርቆት፣ በህገወጥ መስመር ዝርጋታና ቆጣሪ መግጠም እንዲሁም ለባቡር በተዘረጋ ኬብል ላይ በተፈፀመ ስርቆት መሆኑንን አገልግሎቱ ገልጿል፡፡
አገልግሎቱ በመላው ሃገሪቱ ፍትሃዊ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እየሰራ ቢሆንም÷ በየጊዜው እኩይ ዓላማ ባነገቡ ግለሰቦች በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ የሚፈፀሙ ስርቆቶች በአገልግሎት አሰጣጡ እንቅፋት ሆነውብኛል ብሏል፡፡
ህገ ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል ሁሉም ህብረተሰብ በባለቤትነት ስሜት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቱን ሊጠብቅ ይገባልም ነው ያለው፡፡
በ2014 በጀት ዓመት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከ6 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የመሰረተ ልማትና የኃይል ስርቆት እንደተፈፀመበት ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version