አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 8 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቱርክ ፕሬዚዳንት ረጅብ ጠይብ ኤርዶኻን ጋር ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከቱርክና አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን እሳቸውና የልዑካን ቡድናቸው ከፕሬዚዳንት ረጅብ ጠይብ ኤርዶኻን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ማካሄዳቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።
የሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት ሁልጊዜም በመከባበር ላይ የተመሠረተ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ትብብራችን በገንቢ ተሳትፎ ላይ በመመሥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካን ቡድናቸው በሦስተኛው የቱርክ አፍሪካ አጋርነት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ወደ ቱርክ ማቅናታቸው ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢስታንቡል ሲደርሱም የሀገሪቱ ከፍተኛ አመራሮች እና በቱርክ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

68,313
People reached
10,623
Engagements
Boost post
5.5K
211 Comments
266 Shares
Like
Comment
Share
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

