Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የቱርክ አፍሪካ አጋርነት ጉባኤ ለልማት ትብብር የሚጠቅም ዓይነተኛ ዘዴ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሦስተኛው የቱርክ አፍሪካ አጋርነት ጉባኤ ላይ ተሳትፈዋል።
ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን በቱርክ እና በአፍሪካ ሀገራት መካከል የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጠውንና የሚያበረታታውን መድረክ በማስቀጠላቸው አመሰግናለሁ ብለዋል።
እንዲህ ያለው ጉባኤ ለልማት ትብብር የሚጠቅም ዓይነተኛ ዘዴ መሆኑንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተናገሩት።
የቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን በጉባኤው መክፈቻ ላይ የአፍሪካ ሀገራት ስብሰባውን ለመካፈል ወደ ኢስታንቡል በመምጣታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል፡፡
ቱርክ በፈረንጆቹ 2005 የአፍሪካ ዓመት በሚል መሪ ቃል አዲስ ምዕራፍ እንደከፈተች አስታውሰዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ “ ከአፍሪካ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ጋር በእኩልነት እና በወዳጅነት መንፈስ የትብብር ግንኙነታችንን ለማሳደግ ሰርተናል ”ም ብለዋል፡፡
ለአህጉሪቷ ከልክ ያለፈ ንቀት የሚያሳዩ የምዕራባዊያን ሀገራትንም እንደማይቀበሉ ነው የገለፁት፡፡
በፈረንጆቹ 2008 በአህጉሯ ሁለንተናዊ መዋቅር ውስጥ የአፍሪካ ሕብረት ስትራቴጂካዊ አጋር በመሆን የበኩላችንን ተወጥተናልም ብለዋል፡፡
ከ30 የሚበልጡ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በዚህ ጉባኤ ላይ ተሳትፈዋል።
ቱርክ ከአፍሪካ ጋር ያላት ግንኙነት በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ መምጣቱ ይነገራል።
ሀገሪቱ በፈረንጆቹ 2002 ላይ በ12 የአፍሪካ ሀገራት ብቻ ኤምባሲ የነበራት ሲሆን፥ አሁን ላይ ግን በ43 የአፍሪካ ሀገራት ኤምባሲ ከፍታለች።
የዓየር መንገዷም ወደ 60 የተለያዩ የአፍሪካ መዳረሻዎች በመብረር ላይ ይግኛል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version