Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን ከጋሸና እስከ ወልዲያ ያሉ አካባቢዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከጋሸና እስከ ወልዲያ ያሉ አካባቢዎችን ጎበኙ።
በጉብኝታቸው በየከተሞቹ የደረሱ ጉዳቶችን የተመለከቱ ሲሆን÷ የሰሜን ወሎ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ አቡነ ኤርሚያስን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን አነጋግረዋል፡፡
በዚህ ወቅት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በከተማዋ ስለነበረውና ስለሆነው በአቡነ ኤርሚያስ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
አሸባሪው ቡድን በወልዲያና አካባቢው ቆይታው የፈጸማቸውን በደሎችና ህብረተሰቡ ችግሩን ለማለፍ ሲያደርግ የነበረውን ተጋድሎ አቡነ ኤርሚያስ አስረድተዋል፡፡
አቶ ደመቀ በበኩላቸው÷ አቡነ ኤርሚያስ የከተማዋን ሕዝብ በማረጋጋትም ሆነ ጉዳት እንዳይደርስበት ሲያደርጉ ለነበረው ትልቅ ተጋድሎ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በቀጣይ በሚኖረው ሂደት እንደ እስካሁኑ ሁሉ እገዛቸው እንዳይለይ አደራ በማለት የደረሰውን ጉዳት አጣርቶና ለይቶ በማቅረብ ሂደትም እገዛ እንዲያደርጉ አቶ ደመቀ መጠየቃቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version