Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለመከላከያ ሰራዊትና ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ19 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ተቋማት ለመከላከያ ሰራዊትና ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ19 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ፡፡

የተለያዩ ተቋማትና ድርጅቶች ለሀገር መከላከያ ሰራዊትና በወረራዉ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ማቋቋሚያ ከ16 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ድጋፉንም ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ አስረክበዋል፡፡

ድጋፉን ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ፣ እየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርሲቲያን ፣በልሲቲ ነገሳ ትሬዲንግ የግል ድርጅት ፣ባለዛፍ የአልኮልና መጠጥ ድርጅትና ፊቨን ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ናቸው።

በተያያዘ የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊትና ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ3 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ አመራርና ሰራተኞች በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከዚህ ቀደም ድጋፍ አድርገዋል።
በዛሬው እለት ደግሞ ለአገር መከላከያ ሰራዊትና ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ መደረጉን በኮርፖሬሽኑ የማህበራዊ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ወይዘሮ ትእግስት አለማየሁ ተናግረዋል።
የተቋሙ ሰራተኞች የአገርን ሉዓላዊነት እያስከበረ ላለው ሰራዊትና ለተፈናቀሉ ወገኖች አጋርነታቸውን ለማሳየት በራሳቸው ተነሳሽነት ድጋፉን ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል።
የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች በመጀመሪያው ዙር ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸውን ሃላፊዋ አስታውሰዋል።
በቀጣይም ተመሳሳይ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version