ለመከላከያ ሰራዊትና ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ19 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ተቋማት ለመከላከያ ሰራዊትና ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ19 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ፡፡
የተለያዩ ተቋማትና ድርጅቶች ለሀገር መከላከያ ሰራዊትና በወረራዉ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ማቋቋሚያ ከ16 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ድጋፉንም ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ አስረክበዋል፡፡
ድጋፉን ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ፣ እየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርሲቲያን ፣በልሲቲ ነገሳ ትሬዲንግ የግል ድርጅት ፣ባለዛፍ የአልኮልና መጠጥ ድርጅትና ፊቨን ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ናቸው።