አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ አሜሪካ ሀገሪቱን ከአጎዋ ተጠቃሚነት ማገዷን በድጋሚ እንድታጤነው ጠየቀች።
ባሳለፍነው ሳምንት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ኢትዮጵያን ከአጎዋ ማእቀፍ እንድትወጣ በፊርማችው ማፅደቃቸው ይታወቃል።
ይህን ተከትሎ የኢፌደሪ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በፕሬዚዳንት ባይደን ውሳኔ ማዘኑን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ከሶስት ዓመት በፊት የጀመረውን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሪፎርም ለማጠናከር እና ሠላምና መረጋጋትን በሀገሪቷ ለማስፈን እየተንቀሳቀሰ መሆኑን መግለጫው አመልክቷል፡፡
አሜሪካ በሁለቱ ሀገራት መካከል የቆየውን የተጠናከረ ግንኙነት በማጤን የሀገራትቱን የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጠውን የአጎዋ ሥምምነት ወደ ቀድሞው እንድትመልስም መንግስት ጠይቋል፡፡
የኢትዮጵያን ከአጎዋ ተጠቃሚነት መሰረዝ ሀገሪቷ በሰብዓዊ መብት ላይ እየሰራች ያለውን ሥራ የሚያኮስስ እና ወደኋላ የሚጎትትም እንደሆነ መግለጫው አመላክቷል፡፡
በአጎዋ ዕድል በመጠቀም ወደ አሜሪካ ከሚላከው ወጪ ንግድ በሀገሪቷ ላሉ በሺህዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሮ እንደነበረና በዕድሉም ወጣቶች ሴቶች እና ሕፃናት እንዲሁም ቤተሰብ ተጠቃሚ ሆኖ ኑሮውን ሲደጉም እንደነበር በመግለጫው ተነስቷል፡፡
በመሆኑም አሜሪካ ሀገሪቱን ከአጎዋ ተጠቃሚነት ማገዷን በድጋሚ እንድታጤነው ነው የጠየቀው።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!