Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አንዳንድ ምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ስለ ኢትዮጵያ የሚዘግቡበት ሁኔታ የተዛባ ነው – ጣሊያናዊቷ ጋዜጠኛ ፍራንቼስካ ሮቺን

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጣሊያናዊቷ ጋዜጠኛ ፍራንቼስካ ሮቺን አንዳንድ የምዕራባውያኑ መገናኛ ብዙኃን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የሚዘግቡበት ሁኔታ የተዛባ እና ለአንድ ወገን ያደላ መሆኑን ገለጹ፡፡

ፍራንቼስካ ከፋና ጋር በነበራቸው ቆይታ ÷ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ዘጋቢዎች ለአሸባሪው ህወሓት ያደላ አዘጋገብ እንደሚከተሉ ጠቅሰው፥ እንደ ጋዜጠኛ የሁለቱን ወገኖች ቃል ያካተተ እና በትክክል በሀገሪቷ ውስጥ ያለውን እውነታ የሚያሳይ ዘገባ መሥራት እንደነበረባቸው ያነሳሉ፡፡

ጋዜጠኛዋ ሲ ኤን ኤን አዲስ አበባ በህወሓት ቁጥጥር ስር ልትወድቅ መሆኗን መዘገቡ ከሚስተዋለው ነባራዊ ሁኔታ አንጻር የጣቢያውን ብሎም የምዕራባውያኑን መገናኛ ብዙኃን አድልዖ እና የሃሰት ዜና ያጋለጠ ሁነት እንደነበርም አውስተዋል።

ምዕራባውያኑ ስለ ኢትዮጵያ የሚያወጡት መረጃ የተሳሳተ እና ለአንድ ወገን ያደላ መሆኑን ጠቁመው መንግሥት የሚሰጣቸውን መረጃ ከተባለው ዓውድ ውጪ አዛብተው በመተንተን ያቀርባሉ ብለዋል፡፡

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ መረጃ ከመገናኛ ብዙኃኑ ሲሰጠው እንዳለ ከመቀበል ይልቅ እንዴት ብሎ መጠየቅ እና ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት መፈለግ አለበትም ብለዋል ጣሊያናዊቷ ጋዜጠኛ ፍራንቼስካ ሮቺን፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version