አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ውይይት ጀመሩ፡፡
መንግሥት ተገዶ የገባበት የህልውና ጦርነት የመጀመሪያ ምዕራፍ በድል መጠናቀቁን ተከትሎ÷ የተገኙትን ሁለንተናዊ ድሎች ጠብቆ የማስፋትና ወደ ዘላቂ ሰላምና ልማት ማሸጋገር ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
የተገኘውን ድል ተከትሎ ሊመጡ የሚችሉ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሰብአዊና የፀጥታ ፈተናዎችን በብቃት መፍታትና በአግባቡ መምራትም እኩል ትኩረት ያገኛሉ ተብሏል፡፡
በህልውና ጦርነት ሂደት ውስጥ የተገኘው አገራዊ አንድነት ተናቦና ተቀናጅቶ የመስራት ልምድ፣ በጋራ ዓላማ ለጋራ የመስራት ልምድ፣ የአመራር ሁለንተናዊ ተሳትፎና ቁርጠኝነት፣ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሁለንተናዊ ብልፅግና ለመጠቀም በሚያስችል መልኩ የመምራት አስፈላጊነት ላይ ከፍተኛ አመራሩ በጥልቀት ይወያያል መባሉን ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በውይይቱ የድህረ ጦርነት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ የፀጥታና ሰብአዊ ሁኔታዎች በብቃት በመምራት የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ውይይቱ ለ3 ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ይሆናል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

