Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የዳያስፖራውን አገራዊ ተሳትፎ የሚያጎለብቱ የተለያዩ መርሃ ግብሮች ተዘጋጅተዋል-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዳያስፖራውን አገራዊ ተሳትፎ የሚያጎለብቱ የተለያዩ መርሃ ግብሮች መዘጋጀታቸውን ሚኒስቴሩ በሰጠው ሳምንታዊ መግለጫ አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ የ100 ቀናት የስራ ግምገማ ማካሄዱን የገለጸ ሲሆን፥ የተቋሙ የመዋቅር ለውጥ በስኬት ተጠናቋልም ነው ያለው።
አሁን ያለው መዋቅር አገራዊ ክፍለ አህጉራዊ አስቻይ ሁኔታዎችን እና ተግዳሮቶችን ግምት ውስጥ ያስገባ ለውጥ መሆኑንም ገልጿል።
በዚህም ዳያስፖራውን አስተባብሮ ሃገራዊ ጉዳዮችን አንግቦ እንዲንቀሳቀስ ማድረግ መቻሉ የተገለጸ ሲሆን፥ በአሸባሪው የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ በመገንባት ረገድ ዲያስፖራው የጎላ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።
በዚህም ለዳያስፖራው ተሳትፎ ከተዘጋጁት መርሃ ግብሮች መካከል ባዛርና ኤግዚቢሽን፣ የአዲስ አበባ ፖርኮች ጉብኝት፣ የተጎዱ አካባቢዎችን ጉብኝት፣ የገናን በላሊበላ፣ የደም ልገሳ መርሃ ግብር፣ የኢንቨስትመንት ፎረሞች በኦሮሚያ እና በሲዳማ ክልል፣ ዲያስፖራ እንደ እናትና አባት፣ ጥምቀትን በጎንደር፣ የስፖርት ፌስቲቫል የመሳሰሉት እንደሚገኙም ተመላክቷል።
ዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች አሸባሪው ህውሃት በአፋር እና በአማራ ክልሎች የፈጸመውን ወንጀል ሲዘግቡ እንደማይታይ ተነስቷል።
በዚህም የተዛቡ መረጃዎችን ማረም በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ሲምፖዚየም መካሄዱ ተገልጿል።
ከዚያም ባለፈ በአራት ዩኒቨርሲቲዎች የፐብሊክሊክ ዲፕሎማሲ ማዕከላት መመስረቱ ተገልጿል።
ማእከላቱም በአገር አቀፍ ደረጃ ህብረት ፈጥረው ጠንካራ ተግባር ይፈጽማሉ ተብሏል።
በሳምንታዊ የሚኒስቴሩ መግለጫ ላይ የብሄራዊ የምክክር መድረክ አላማ ሃገራዊ መግባባትን መፍጠር መሆኑ ተመላክቷል።
በዚህም ከታችኛው የማህበረሰብ እርከን ጀምሮ እስከላይኛው እርከን ያሉ አካላት እንደሚሳተፉበት ተገልጿል።
በባህሬን እና በአልጀሪያ የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ከአገራቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ውይይት ማካሄዳቸውም ተገልጿል።

ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ የሚያራምዱትን የተዛባ ፖሊሲ አስተካክለው ወደ ትክክለኛ የግንኙነት መስመር እንዲገቡ በ2022 ሰፊ ዲፕሎማሲያዊ ስራ ይሰራልም ተብሏል።

የውጭ ግንኙነት መርሆች ሁለት መሆናቸውን የጠቀሰው መግለጫው ፥እነርሱም  የአገሪቱን ሉአላዊነት ማስጠበቅና  የዜጎችን መብቶች ማስጠበቅ ዋነኞቹ መሆናቸው ተመላክቷል።

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ጀፍሪ ፌልትማን ከኢትዮጵያ ውጭ ከሌሎች አገራት መሪዎች ጋር የሚያደርጉት ንግግር ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ መሆኑም በመግለጫው ተመላክቷል።

ከህዳሴው ግድብ ጋር ተያይዞ ሲካሄድ የነበረው ሶስትዮሸ ድርድር በሱዳን አለመረጋጋት የተነሳ መቀጠል አለመቻሉ  ተነስቷል፥ በሱዳን እየታየ ያለው አለመረጋጋት አፍሪካዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ኢትዮጵያ ድጋፏን  እንደምትቀጥል ተገልጿል።

 

በወንደሰን አረጋኸኝ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 1 person and sitting
10,912
People reached
721
Engagements

-2.7x lower

Distribution score
Boost post
435
12 Comments
11 Shares
Like

 

Comment
Share
Exit mobile version