አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው እና ዘራፊው የህወሓት ቡድን በሀይቅ ከተማ በሚገኘው የሎጎ ሀይቅ ቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጅ 1 ቢሊየን ብር የሚገመት ዘረፋ እና ውድመት ማድረሱን የኮሌጁ ዲን አቶ ተመስገን ጸጋው አስታውቀዋል፡፡
ቡድኑ በአካባቢው በወረራ በቆየበት ወቅት ካደረሰው ሰብአዊ ጉዳት በተጨማሪ፥ ተተኪ ትውልድ የሚማርበትን የትምህርት ተቋም አውደርሟል ብለዋል ዲኑ፡፡
ኮሌጁ ለአምባሰል፣ ተሁለደሬ እና ወረባቦ ወረዳዎች እንዲሁም ሀይቅ ከተማ አገልግሎት ይሰጥ የነበረ ተቋም ነው።
ዘራፊው የህወሃት ቡድን የኮሌጁን ንብረት የቻለውን በመዝረፍ ያልቻለውን አገልግሎት እንዳይሰጥ በማውደም የትምህርት አገልገሎት መስጠት በማይችልበት ደረጃ አድርሶታል።
በዚህም ምክንያት ኮሌጁ አሁን ላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር እንደማይችል የኮሌጁ ዲን ጨምረው አስታውቀዋል።
በተመሳሳይ የሽብር ቡድኑ በይሀቅ ከተማ አራት ሴክተር መስሪያ ቤቶች የነበሩበትን የመንግስት ተቋም ሙሉ በሙሉ በእሳት አውድሟል፡፡
ከተማዋን የተመለከቱ ሰነዶች እና ልዩ ልዩ ውሳኔዎች በአሸባሪው ቡድኑ የወደሙ ሲሆን፥ በዚህም የከተማዋ የምስረታ ታሪካዊ ቃለጉባኤ ጨምሮ የእስካሁን ታሪክ በሰነድነት የሚያስረዱ ሰነዶች ወድመዋል።
በለይኩን ዓለም
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

