አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፄ ቴዎድሮስ ሹርባ (ቁንዳላ)የሽኝት መርሃ ግብር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
በመርሃ ግብሩ መሰረትም ከብሔራዊ ሙዚየም ተነስቶ ወደ 4 ኪሎ አደባባይ ሽኝቱ ይደረጋል፡፡
በመቀጠልም የአፄ ቴዎድሮስ ሹርባ (ቁንዳላ) ወደ ጎንደር የሚሸኝ ሲሆን ÷በጎንደር ከተማ ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግለት ከጎንደር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በመዲናዋ እየተደረገ በሚገኘው ሽኝት መርሃ ግብርም የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ጨምሮ አባት አርበኞች ፣ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ፣ታዋቂ ግለሰቦችና ሌሎች ተገኝተዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

