የአፄ ቴዎድሮስ ሹርባ(ቁንዳላ) የሽኝት መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው
በመርሃ ግብሩ መሰረትም ከብሔራዊ ሙዚየም ተነስቶ ወደ 4 ኪሎ አደባባይ ሽኝቱ ይደረጋል፡፡
በመቀጠልም የአፄ ቴዎድሮስ ሹርባ (ቁንዳላ) ወደ ጎንደር የሚሸኝ ሲሆን ÷በጎንደር ከተማ ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግለት ከጎንደር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በመዲናዋ እየተደረገ በሚገኘው ሽኝት መርሃ ግብርም የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ጨምሮ አባት አርበኞች ፣ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ፣ታዋቂ ግለሰቦችና ሌሎች ተገኝተዋል፡፡