Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የ100 ቀናት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ ጠ/ሚ ዐቢይ በተገኙበት በህዳሴ ግድብ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሁሉም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የ100 ቀናት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በህዳሴ ግድብ መገኛ በሆነው ጉባ እየተካሄደ ይገኛል።
 
ኢኮኖሚው በዚህ ዓመት በርካታ ፈተናዎች ቢደቀኑበትም በዋና ዋና ማክሮ ኢኮኖሚ ዘርፎች ዕድገት መመዝገቡ በግምገማው ላይ ተጠቁሟል።
 
በሪፖርቱ ኢኮኖሚው በዚህ ዓመት በርካታ ፈተናዎች ቢደቀኑበትም በዋና ዋና ማክሮ ኢኮኖሚ ዘርፎች ዕድገት መመዝገቡ በግምገማው ላይ ተጠቁሟል።
 
በግምገማው በሸቀጦች የወጪ ንግድ ባለፉት አምስት ወራት 1 ነጥብ 64 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 1 ነጥብ 61 ቢሊየን ዶላር ማግኘት ተችሏል መቻሉ ተጠቁሟል፡፡
 
ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ21 ነጥብ 3 በመቶ እድገት አስመዝግቧል ነው የተባለው፡፡
 
በሌላ በኩል 824 ሚሊየን ዶላር የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት መሳብ እንደተቻለ ተገልጿል፡፡
 
በሌላ በኩል ባለፉት 3 ወራት በግብርናው ዘርፍ ጥሩ አፈፃፀም መመዝገቡ የተገለፀ ሲሆን፥ የምርት አሰባሰቡም ስኬታማ ነበር ተብሏል፡፡
 
በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት 336 ነጥብ 45 ሚሊየን ኩንታል የሰብል ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ 301 ነጥብ 47 ሚሊየን ኩንታል የሰብል ምርት መሰብሰብ ተችሏል ነው የተባለው ፡፡
 
ታክስ እና ታክስ ካልሆኑ ግኝቶችና የሃገር ውስጥ ገቢ ደግሞ 143 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር መሰብሰብ እንደተቻለ ታውቋል፡፡
 
የበጀት ዓመቱ ኢኮኖሚ ተስፋ ሰጪ ቢሆንም ኢትዮጵያ ተገዳ የገባችበት ጦርነት ግን ፈተናዎችን መደቀኑ እንደማይቀር የዘርፎቹን አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍፁም አሰፋ ተናግረዋል።
 
ለዚህም ያለውን የውጭ ምንዛሬና የሃገር ውስጥ ፋይናንስ በአግባቡ እና ቅድሚያ ለሚሰጠው ዘርፎች ማዋልና ውጤታማ የአጠቃቀም አሰራርን መዘርጋት ያስፈልጋል ብለዋል ሚኒስትሯ ባቀረቡት ሪፖርት፡፡
 
የግምገማው ዓላማ ችግሮችን ማረም፤ የተገኙ ውጤቶችን ማጽናት እና በላቀ ሁኔታ ማስቀጠል መሆኑም ተገልጿል።
 
 
 
በአልአዛር ታደለ
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
 
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version