አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዚህ ዓመት በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተውን የዲፕሎማሲ ጫና ለመቋቋም የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ እንደነበሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ።
በተሰራው የዲፕሎማሲ ስራም የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ጥረት መደረጉን ገልፀዋል።
ከዚህ ባለፈ የኢትዮጵያን እውነት ለአለም ለማሳወቅ በተሰራው ስራ በአገር ውስጥ እና በውጭ ያሉ ዳያስፖራዎች የሰሩት ስራ ትልቅ አቅም የፈጠረ እንደነበር ተናግረዋል።
ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ እንዲሁ ጉዳዩን የአለም አቀፍ ጫና መፍጠሪያ ለማድረግ ቢሞከርም ጉዳዩ በአፍሪካ ማዕቀፍ ውስጥ እንዲታይ ለማድረግ ውጤታማ ስራ መሰራቱን አቶ ደመቀ ገልጸዋል።
ኢትየጵያን በተሳሰተ መንገድ ለመፈረጅ እና ከተፈጥሮ ሃብቷ እንዳትጠቀም ለማድረግ የሚሰሩ ሀገራት የሚሄዱበት የተለያየ የሴራ እንቅስቃሴም ከህዳሴ ግድብ ጋር የተያያዘ መሆኑን ነው አቶ ደመቀ የገለፁት።
ይህንንም ሴራ በመስበሩም ኢትዮጵያውያን ስኬታማ መሆናቸውን አመልክተዋል።
በአልአዛር ታደለ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!