Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ያስቀመጡትን ግብ ከማሳካት አንፃር ከፍተኛ ለውጥ አስመዝግበዋል- ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በየዘርፋቸው ለመምታት ያስቀመጡትን ግብ ከማሳካት አንፃር ከፍተኛ ለውጥ ማስመዝገባቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።
 
የሁሉም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የ100 ቀናት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት በህዳሴ ግድብ መገኛ በሆነው ጉባ እየተካሄደ ይገኛል።
 
በግምገማውም የተገኙ ውጤቶችን ማጽናት እና በላቀ ሁኔታ ማስቀጠል የሚቻልበትን እንዲሁም ካጋጠሙ ተግዳሮቶች እድሎችን መፍጠር የሚቻልበትን አቅጣጫ ማስቀመጡንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባወጡት ፅሁፍ አመልክተዋል።
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
Exit mobile version