Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአፍሪካ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለህብረቱ ጉባኤ አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል

የአዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤና በ40ኛው የአስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል።

ዛሬም የዚምባብዌ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፍሬድሪክ ሻቫ እና የሳዖቶሜና ፒሪንሲፔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤዲቴ ራሞስ ቴንዡዋ ገብተዋል።

ሚኒስትሮቹ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ጉዳዮች ሹም አምባሳደር ፈይሰል አልይ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የሁለቱም ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በጉባኤው ለመሳተፍ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣታቸው ከፍተኛ ኩራትና ደስታ እንደተሰማቸው ተናግረዋል።

35ኛው የህብረቱ ጉባኤና 40ኛው የአስፈፃሚ ምክር ቤቱ ስብሰባ ኢትዮጵያ መልካም ገፅታዋን ለአለም የምታሳይበት መልካም አጋጣሚ መሆኑን አምባሳደር ፈይሰል አልይ መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version